Fayyaan Mataa, Fayyaa Waa Maraa ti!

ስምንት የካርታ መረጃ ያለው የኦሮሞ ሀገር::

በብሔራዊና በጎሳዎች ደረጃ የተሰሩ ካርታዎች።

በአበሲኒያ ዘመን የመሣፍንት ጦርነት እየተባለ የሚጠራዉ አብዛኛዉ የሃይማኖት ጦርነት ነበር፡፡እትዮጵያ ለዘመናት ሰላም አጥታ እየተበጠበጠች ሕዝቦቿ ደምእምባ እያለቀሱ የምትኖረዉ ምንጩ ሃይማኖት ነዉ፡፡ከ16ኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ አበሲኒያን ሲያሰታጥቁ የኖሩና እስከ ዛሬ ድረስ የኢትዮጵያ ገዥመደቦችን እያስታጠቁ በሥልጣን ላይ የሚጠብቁ የዉጭ ኃይሎች ምስጥሩ ሃይማኖት ነዉ፡፡ኢትዮጲያ በሃይማኖት ጦርነት ተጸንሳ በጠመንጃ ተወልዳ በጠመንጃ እየተጠበቀች የምትኖር ሀገር መሆኗን ታሪኳ ይመሰክራል፡፡በአጼ ዮሐንስ4ኛ (ካሣ ምርጫ)ና በአጼ ቴዎድሮስ የተጀመረዉ የሃይማኖት ጦርነት ዋሎ የኦሮሞ ሀገር እንዲይዙ አደረጋቸዉ፡፡በእነዙ የተጀመረዉ መስፋፋት በአጼ ምንሊክ ከግብ ደርሶ ኦሮሞ ለቅኝ አገዛዝ በርነት የተዳረገዉ ምንጩ ሃይማኖት ነዉ፡፡ከትዉልድ ትዉልድ በዉጭ ኃይሎች እየተደገፉ እሰኑ ብቻ እየታጠቁ እየነገሱ የሚኖሩት “የክርስቲያን ዴሴት ኢትዮጵን ከእስላሞች ወረራ እንጠብቃለን እያሉ” ነዉ፡፡

በሃይማኖት ምክንያት የማያቋርጥ እርዳታና ድጋፍ እያገኙ የቅኝአገዛዝ ቀምበራቸዉን እያጠበቁ የተጨቆኑ ሕዝቦችን አፈር እያስጋጡ ይገዛሉ፡፡ የሐበሻ እሌቶች እዉነቱን ለመደበቅ ቅኝገዥና ቅኝተገዥ የሚባል የለም ይላሉ፡፡አንባቢያን የቅኝአገዛዝ ታሪክ መነሻና መድረሻ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲታገኙ የሚከተሉ መረጃዎችን ልብ ብላችሁ እንድትአነቡ እጋብዛችኋለሁ፡፡አንድ ሀገር በወረራ የሌላ ሕዝብ ሀገር ይዞ ወደግዛቱ ከአጠቃለለ ቅኝገዥ ነዉ፡፡ አንድ ሕዝብ ሀገሩ ተይዞ ለኡአላዊነቱ ተገፎ ህልዉናዉ ተረግጦ ከተገዛ ቅኝተገዥ ነዉ፡፡እነዚህ ሁለት ምክንያቶች የቅኝ ተገዥነትና የቅኝገዥነት ማረጋገጫ ማሃተም ናቸዉ፡፡አበሲኒያ ኦሮሞና ደቡብ ሕዝቦችን በጦር ኃይል ጨፍልቃ እትዮጵያን የመሠረተች መሆኗን የሐበሻ ምሁራኖች ሳይቀሩ ይመሰክራሉ፡፡ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማሪያም አሰብ የማናት በሚለዉ መጽሐፉ ገጽ 1 ላይ ይህንን አረጋግጧል፡፡

“የአወቀ ይመስክር፤የአየ ይናገር እንደሚባለዉ” የሐበሻ ምሁራኖች የሚሰጡት ምስክርነት ኢትዮጲያ ቅኝገዥ ለመሆኗ ተጨማሪ መረጃ ነዉ፡፡ ሌላ መረጃ ይመልከቱ፡፡“የዛሬዋ እትዮጵያ ግዛት የተፈጠረችዉ የሌሎች ሕዝቦችና የኦሮሞ ሀገር በመዋጥ ነበር፡፡አበሲኒያ ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት፤ከደቡብ ሱዳን እስከ ሶማሊ ድረስ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦችና በአሁኑ ሰሜን አዲስ አበባ ይኖሩ የነበሩ ነጻ ግዛቶችን በመዉረር ወደ ግዛቷ አጠቃለለች፡፡በዚያን ዘመን በኃይል የተማረኩ ሕዝቦች ለብዙ ዓመታት የራሳቸዉ መንግሥት መስርተዉ በነጻነት ይኖሩ ነበር”፡፡A Galla Monarchy መግቢያ ገጽ 0፡፡

ኦሮሞና ደቡብ ሕዝቦች ቅኝተገዥ ለመሆናቸዉ አበሲኒያ ከአዉሮፓዊያን ጋር የተፈራረመችዉ ሀገር የመጠቅለል ዉል እንደሚከተለዉ ያረጋግጣል፡፡“እንግሊዝ ለአበሲኒያ የወሰነችዉን ዳር ድምበር ኢጣሊያና ጀርመን አልተቀበሉም፡፡ በ1885 Territorial Arrangements with Germany, Italian and Abyssinia (በጀርመን ኮሎኒያል ፖሊሲ፤በኢጣሊያና በአበሲኒያ የድምበር ማስተካከያ ሰነድ ላይ አዲስ ዉል ተፈረመ)፡፡ እንግሊዝ ለአበሲኒያ የከለለችውን ዳርድምበር ጀርመንና ኢጣሊያን ያልቀበሉበት ምክንያት የቦረና ክልል ቆርሳ ወደ ቅኝ ግዛቷ ኬንያ ለማጠቃለል ካርታ በማውጣቷ ነበር። በዚህ ተቃውሞ መሠረት ቦረና በአበሲኒያ ቅኝ አገዛዛዝ ስር እንዲሆን ተወስኖ የዛሬው ኢትዮጲያ አካል ሆነ። በዚህን ግዜ ኦሮሞ በምንሊክ ተመትቶ ተበታትኖ ይኖር ነበር። በአበሲኒያ ኮድ 445 ላይ የኦሮሞ የደቡብ ሕዝብና የኡጋዴን ግዛት በአበሲኒያ ስር እንዲጠቃለሉ ተወስኖ የዛሬዋ ኢትዮጲያ ግዛት ተፈጠረ”፡፡ The Map of Africa 1967 ገጽ 338-9

የዉል ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ የምንሊክ ጦር መሃንዲስ የነበረዉ የፈረንሳይ ኮሎኔል በአበሲኒያ ኮድ 445 መሠረት የዛሬዋ አትዮጵያ ካርታ ሰርቶ ለምንሊክ አስረከበ፡፡ጀርመንና ኢጣሊያን ሉዓላዊ የነበራቸዉ ሕዝቦችን በአበሲኒያ ስር እንዲጠቃለሉ ያዳረጉበት ዋናዉ ዓላማ ፓጋንና እስላም የሚባሉ ሕዝቦችን ሃይማኖት ለዉጠዉ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮችን የክርስቲያን ቀጠና ለማድረግ የታሰበ እንደሆነ ከዚያን ወዲህ ሃይማኖት ለማሰውፋፋት የተወሰዱ እርምጃዎች ይመሰክራሉ ፡፡ሁለተኛዉ ዓላማቸዉ ምንልሊክን እንደቡቺላ ተጠቅመዉ ቀጠናዉን ተቆጣጥረዉ የተፈጥሮ ሃብት እየበዘበዙ ለመኖር ነበር፡፡በዉጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ቅኝተገዥ ሕዝቦች በሀገራቸዉ ላይ እየተዋረዱ እየታረዱ እንደሳር እየታጨዱ ፍጅት እየተፈጸመባቸዉ እየፈሰሰ የሚኖረዉ ደማቸዉ ተመልካች አጥቶ ይኖራል፡፡ ምክንያቱም ከዉጭ ደጋፊ ኃይል በማጣታቸዉና ከዉስጥ የነቃ የተደራጀ የታጠቀ በአንድነት ተነስቶ የቅኝ አገዛዝ ቀምበር ሰብሮ የአበሲኒያ ኮድ 445 ሰርዞ ነጻሚያወጣች ኃይል በመጥፋቱ ነዉ፡፡

በአጼ ዮሐንስና በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተካሄደዉ የሃይማኖት ጦርነት በምንሊክ ዓላማቸዉ ከግብ ደረሰ፡፡ የዋቄፈታና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ወደ ክርስቲያን ለመለዉጥ በታቀደዉ መሠረት ምንሊክ “ከድል ማግስት ባላባቶቹ አብያተ ክርስትያን እንዲያሳንጹ በአዋጅ አስነገረ፡፡በዚህ መሠረት “በርከት ያሉ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት በተማረኩ (በቅኝተገዥ ሕዝቦች ሀገር) ተቋቋሙ”፡፡ቅንፍ የራሴ፡፡ ፍስሐ ያዜ ገጽ 429

ኦሮሞ በቅኝከመያዙ በፊት የራሱ ሀገር ካርታ ነበረዉ፡፡

“ምንሊክ የኦሮሞ ሃብታም ሀገር ወግቶ ደቡብና ምዕራብ ግዛቶቹን ተቆጣጥሮ እንዲይዝ ፈረንሣይ በጥንቃቄ ትመክረዉ እንደነበር” ታሪከ ይመሰክራል፡፡ A History of Ethiopia page 139 by A. H. M Jones and Elizabeth Monroe፡፡ ምንሊክ በፈረንሣይ ኮሎኔል ጦር መሃንዲስነት እየተመራ ኦሮሞን ወግቶ ቅኝ ከመያዙ በፊት ሉዓላዊ ሀገር የነበረዉ መሆኑ ብዙ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ ኦሮሞ ቅኝ ተገዥ ነኝ ሲል የሐበሻ እሌቶች “የነጻ ሀገራችሁ ካርታ የትአለ አቅርቡ” እያሉ ያሾፋሉ፡፡ ምክንያቱም በአሲኒያ አሻጥርና በዉጭ ኃይሎች አቀነባባሪነት የሀገሩ ዳር ድምበር እንዳይታወቅ ካርታዉ መቃብር ዉስጥ መደበቁን ያዉቃሉ፡፡ሰዉ የቀበረዉን ጊዜያወጣል፤በተንኮል የተሸፈነዉን ታሪክ ያግልጣል፡፡ጊዜና ታሪክ ዘለዓለም ፍርድ እየሰጡ ይኖራሉ፡፡ኦሮሞ በገዳ መንግሥታዊ አገዛዝ የሚተዳደር ለኡአላዊ ሀገር የነበረዉ መሆኑን 9 መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡

A) ከወደታች የካርታ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ከ8000 B.C ጀምሮ እስከ 19ኛ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ ኤርትራ፣ጂቡቲ፣እትዮጵያ፣ሱማሌያ የኩሻይት ሀገር እየተባሉ ይጠሩ እንደ ነበር ካርታ ያረጋግጣል፡፡በተለያየ ጊዜ በአቀረብኳቸዉ መረጃዎች መሠረት የኩሽ ሀገር እየተባለ የሚጠራዉ የኦሮሞ ሀገር ነዉ፡፡ኩሻይት ማለት ኦሮሚያ ማለት ነዉ፡፡

B) በ16ኛ ክፍለ ዘመን አፍሪካ በጎሣ ካርታ ይታወቅ በነበረበት ወቅት ኦሮሞ በጎሣዎቹ ላይ የተመሠረተ ነጻ ሀገር ነበረዉ፡፡C) በቅኝ አገዛዝ ላይ የተመሠረተ የዛሬዉ የአፍሪካ ፖለቲካ ካርታ ሳይፈጠር የጋላ ሀገር የሚል ካርታ ነበረ፡፡D) በአበሲኒያ ወረራ ሀገሩ ከመዋጡ በፊት ሉዓላዊ ሀገር ነበረዉ፡፡በአጠቃላይ የኦሮሞ ሀገር በእትዮጵያ ቀሚስ ስር ሉዓላዊነቱ ተቀብሮ የሚኖር መሆኑን 9 የካርታ መረጃዎች ከወደታች ያረጋግጣሉ፡፡

1) በጥንት ዘመን ከኑቢያ እስከ ሶማሊ ድረስ ሀገሩ የኩሻይት ግዛት እየተባለ ለመጠራቱ Atlas of world human Journey ይመልከቱ፡፡

2) ከ8000 B.C ጀምሮ እስከ 19ኛ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ በአፍሪካ ካርታ ማፕ 20 አንስቶ 70 ገጽ ድረስ የኩሽ ሀገር እያለ ሲጠራ የኖረዉ በመጨረሻ የጋላ ሀገር ብሎ ደመደመዉ፡፡ይህ ሰነድ የኩሽ ሀገር የሚባለዉ የኦሮሞ ሀገር መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ታሪካዊ ማፖቹን ከዚህ ታሪክ መጨረሻ ላይ በተከታተይ ይመልከቱ፡፡ መረጃ The penguin Atlas of African history 1995 map 20, 22, 28, 34 ,40 ,54 by Allen Lane

3) የዛሬዉ የኦሮሚያ ካርታ ከ1965 በፊት ጀምሮ የነበረ መሆኑን The Galla of Ethiopia the Kingdom of Kaffa and Janjaro 1955 map 1 by Huntingford and George Wynn Breton ተመልከቱ፡፡

4) በቅኝ አገዛዝ ላይ የተመሥረተ የዛሬዎቹ አፍሪካ ሀገሮች ካርታ የተሰሩት በ1885 ነበር፡፡ የአፍሪካ ካርታ ከመሰራቱ 239 ዓመት በፊት (በ16ኛ) ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኦሮሞ የሀገር ካርታዎች የነበረዉ መሆኑን በእንግሊኛ የተጻፈዉን ሰነድ ተመልከቱ፡፡ ይህ ሰነድ ከላይ ከ1 እስከ 4 ተራ ቁጥር ለተጠቀሱ መረጃዎች ማረጋገጫ ማህተም ይሆናል፡፡

5) Maps of Gallaa land. There are three copies of the map drawn by Almeida to illustrate his history: (6) British Museum Add MS. (Cod) 9861, reproduced by Beccari (RASO;I and V) (7) Brit.Mus.Add.MS. 5027; and (8) school of Oriental and African Studies MS 11966, reproduced by Buckingham and Huntingford .None of this dated, but they were made before 1646 and earliest maps which show the distribution of Gallaa. (9) Ludolf’s map (1683), based on that of Telles (1660) itself complied from Almeida. The Galla of Ethiopia the Kingdom of Kafa and Janjero by G.W.B Huntingford page 96

በእንግሊዘኛ ተጽፎ የቀረበዉ ታሪክ በአማሪኛ ሲተረጎም የጋላ ሀገር ካርታ ተመልከቱ እያለ እንደሚከተለዉ መረጃ ያቀርባል። በደራሲ አላማይዳ በተዘጋጀዉ ሶስት መረጃዎች መሠረት የኦሮሞ (ጋላ) ሀገር ካርታ ነበረዉ፡፡በተጨማሪ በ1660ና በ1683 ደራሲ ሉዶልፍና ቴሌስ ማረጋገጫ ሰጥቶበታል፡፡ከ1646 A.D በፊት የተሰሩ አራት ካርታዎች በተለየዩ ሶስት ኮዶች ተመዝግበዉ በእንግሊዝ ሙዚየም እስከ ዛሬ ድረስ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ከላይ በቀረቡ መረጃዎች መሠረት የኦሮሞ ኢምፓየር እራሱን ያቻለ የሀገር ካርታ ነበረዉ፡፡በጥልቅ ጉድጓድ ተቀብሮ የኖረዉ የኦሮሞ ሀገር ካርታ ከመቃብር ወጥቶ እየተናገረ ነዉ፡፡ኦሮሞ ሀገር የለዉም መጤ ነዉ እያሉ የሕዝብ ጆሮ ሲያደነቁሩ የሚኖሩ ደናቁርት ምሁራን ከዚህ በኋላ ከትዉልድ ትዉልድ መተንፈስ አይችሉም፡፡ ኦሮሞ የሀገሩ ካርታ ተደብቆ ቅኝተገዥ መሆኑን መካድ አይችሉም፡፡ በጠርነት የአንድ ሕዝብ ዳር ድምበር አፍርሶ ካርታዎቹን ቀብሮ ከራሱ ሀገር ጋር የሚቀላቅል ወራሪ ቅኝገዥ ነዉ፡፡

በ1884-85 የአዉሮፓ ቅኝገዥዎች በብሔሮችና በጎሣዎች ላይ ተመስርቶ የኖረዉን የአፍሪካ ሀገሮች ዳርድምበር አፈራርሰዉ በቅኝአገዛዝ ከያዙት ሀገር ቀላቅለዉ አዲስ ካርታ ሰርተዉ አቀረቡ፡፡የዛሬዉ የአፍሪካ ዳር ድምበር ቅኝገዥዎች በያዙት ሀገር ካርታ ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡በ1960 የተባባሩት መንግሥታት ቅኝተገዥዎች ነጻ እንዲወጡ በአወጀበት ወቅት ያስተላለፈዉ ዉሳኔ ቅኝተገዥዎቹ ነጻ ሲወጡ በያዙት ሀገር ድምበር ይጸናሉ ስለአለ ወደጥንቱ ዳር ድምበራቸዉ ሊመለሱ አልቻሉም፡፡የአፍሪካ የዘመናት ጦርነት ምንጩ ቅኝገዠዎች ቀብረዉት የሄዱ የደር ድምበር ፍለሰትና በባህል በታሪክ በሃይማኖት በዘር የማይተዋወቁ ሕዝቦች በተሰራዉ በአዲሱ ሀገር ካርታ ዉስጥ በደባልነት አብረዉ እንዲኖሩ በመደረጉ ነዉ፡፡

ምንሊክ እንደ አዉሮፓ ቅኝገዥዎች የኦሮሞ ሀገር የደቡብ ሕዝዝቦችን ዳርድምበር አፈራርሶ ከአበሲኒያ ጋር አዋህዶ አዲሲ የኢትዮጲያ ካርታ አስርቶ ለዘመናት ከአማራ ጋር ሲዋጉ የኖሩ ጠላታም ሕዝቦች በደባልነት አብረዉ እንዲኖሩ አደረገ፡፡ በኢትዮጲያ የዘመናት ጥላቻ ጭቅጭቅ ጠላትነት ግጭት ምንጩ እንደ እባብና ጉርጥ ጠላታም ሆነዉ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች በቅኝ አገዛዝ ሰንሰለት ታስረዉ ከሚወጓቸዉ ወገኖች ስር በባርነት እንዲኖሩ በመደረጉ ነዉ፡፡ የአዉሮፓ ቅኝገዥዎች የሕዝቡን ቋንቋና ብሔራዊ ሥም ቀይረዉ የሀገር የወንዝ የተራራ ሥም ለዉጠዉ በራሳቸዉ ማንነት እንደ መሠረቱ ሁሉ፤ ኢትዮጵያ የኦሮሞና ደቡብ ሕዝብ ብሔራዊ ሥም የሀገር መጠሪያ የተራራ የወንዝ ሥም ለዉጣ በአማራ ማንነት ሰር አደረገች፡፡በእነዚህ ተጨባጭ መረጃዎች መሠረት በኢትዮጲያና በአዉሮፓ ቅኝገዠዎች መካከል የተግባር ልዩነት የለም፡፡

ከዚህ በላይ የቀረቡ ግዙፍ መረጃዎች ተቀብረዉ የኦሮሞ ሉዓላዊነት በእትዮጵያ ቀሚስ ስር ተደብቆ በቅኝ አገዛዝ ስር እየተረገጠ ይኖራል፡፡ይህ እጅግ በጣም ያሳዝናል ያስለቅሳል፡፡ ይህ ከመቃባር የወጣዉ አስደናቂ ታሪክ በሕይዎት ያሉ ኦሮሞዎችን ብቻ ሳይሆን ለነጸነት ሲታገሉ የተሰዉ ጀግኖች የሚሰሙ ቢሆን ከመቃብር ዉስጥ ቀስቅሶ እንደ ገና ለትግል ያሰልፋቸዋል፡፡ በኦሮሞ ነጻነት ትግል ፊት ቁሞ ብሔርተኞቹን እየሰለለ ለአደጋ እያገለጠ የሚገኘዉ ኦፕዴኦን ሳይጨምር ይህ ታሪክ ጀግኖችን ብሔራዊ ስሜት ቀስቅሶ በማሸፈት ለወሳኝ ትግል እንደሚያዘጋጅ እርግጣኛ ነኝ፡፡የእትዮጵያ ቀሚስ ተገልጦ ቢታይ የኦሮሞ ሀገር ካርታ ብቻ አይደለም ተጋልጦ የሚታየዉ፡፡ ከምንሊክ ዘመን ጀምሮ እስከ ወያኔ አገዛዝ ድረስ በግፍ በሀገራቸዉ ላይ የተጨፈጨፉ አጽማቸዉ እንደተራራ ተከምሮ ይተያል፡፡ እየፈሰሰ የሚኖረዉ ደማቸዉ እንደጎርፍ ይፈሳል፡፡ይህ አሰዛኝ ታሪክ የቅኝአገዛዝ ያስከተለዉ ወርዴ ታሪክ ነዉ፡፡

የተደበቀ የቅኝ አገዛዝ ምስጢር

የሐበሻ ምሁራኖች ከላይ በሰጡት የምስክር ቃልና በተጠቀሱ ብዙ ተጨባጭ መረጃዎች መሠረት ኦሮሞና ደቡብ ሕዝቦች ቅኝተገዥ ናቸዉ፡፡ የቅኝ አገዛዝ አመሰራረት ዘዴ በአራት መደብ ይከፈላል፡፡ወራሪ፣ሰፋሪ፣ተስፋፊና ስዉር ቅኝገዥ ተብሎ ይታወቃል፡፡ኦሮሞና ደቡብ ሕዝቦች ቅኝ የተገዙት በሰፋሪዎች፤ በተስፋፊዎችና በስዉር ቅኝገዥዎች አይደለም፡፡ለቅኝ አገዛዝ ዋና ምክንያት በሆነዉ በወረራ ነዉ፡፡እዚህ ላይ ተጨባጭ መረጃ ተመልከቱ፡፡እንግሊዝ ፈረንሣይ፣ጀርመን ፣ ኢጣሊያን፣ፖርቱጋል፣እስፔይን፣ቤልጅግ አብዛኞቹ አፍሪካን ቅኝተገዥ ያደረጉት በጠንጃ አፈሙዝ ነበር፡፡ ምንሊክ ኦሮሞና ደቡቡቦችን ቅኝተገዥ ያደረገዉ በጠመንጃ አፈሙዝ ነዉ፡፡ ስለዚህ በእትዮጵያና በአዉሮፓዊያን ቅኝአገዛዝ መካከል ምንም ልዩነት የለም፡፡ልዩነታቸዉ የአዉሮፓ ቅኝተገዥዎች ነጻሲወጡ የኢትዮጵያ ቅኝተገዥዎች ግን እስከ ዛሬድረስ በባርነት እየተረገጡ መኖራቸዉ ነዉ፡፡ በግልጽ መታወቅ ያለበት በጦርነት የሰዉ ሀገር የያዘ ወራሪ ቅኝገዥ ሲሆን፤ በኃይል የተያዘዉ ሕዝብ ቅኘተገዥ ነዉ፡፡

በ1884-85 የምዕራብ አዉሮፓ ሀገሮች በጀርመን በርሊን በአደረጉት ስብሰባ አፍሪካን ቅርጫ ለመቀራመት ተስማሙ፡፡ በ1960 ታህሣሥ 14 ቀን የተበባሩት መንግስታታ በአደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ በዉሳኔ 1514 መሠረት የአፍሪካና የኤሽያ ቅኝተገዝ ሕዝቦች ነጻ እዲወጡ አዋጅ አስተላለፈ፡፡በዚህ አዋጅ መሠረት ቅኝተዥዎች ነጸነታቸዉን ተቀዳጅተዋል፡፡ነገር ግን በ1885 በጀርመን ኮሎኒያል ፖሊሲ፤በኢጣሊያና በአበሲኒያ የድምበር ማስተካከያ ሰነድ 445 መሠረት ኦሮሞ፣ጋምቤላ ኡጋዴንና ደቡብ ሕዝብ እስከ ዛሬድረስ በኢትዮጲያ ቅኝአገዛዝ ስር ተጨቁነዉ ይኖራሉ፡፡በአዉሮፓና በኢትዮጲያ ቅኝአገዛዝ ዘዴ መካከል ልዩነት ከሌለ በተባበሩት መንግሥታት አዋጅ መሠረት ቅኝተገዥዎቹ ነጻነት ይገባቸዋል፡፡የኤርትራ ነጻነት በተባበሩት መንግሥታት የተደገፈዉ በአወጁ ህግ መሠረት ነዉ፡፡በዚህ ታረካዊ መረጃ መሠረት ኦሮሞና ሌሎች ጭቁን ሕዝቦች የሚያካሄዱት ነጻነት ትግል ፍትሃዊና ህጋዊ ስለሆነ የዓለም ሕዝብ ልደግፋቸዉ ይገባል፡፡

እንደዚህ ሲል ሕዝቦቹ ተገንጠልዉ የራሳቸዉ መንግሥት መስርተዉ ይኑሩ ማለቴ አይደለም፡፡ ተፈቃቅሮ ተከባብሮ ተስማምቶ በንድነት በነጻነት አብሮ መኖር አስፈላጊ ነዉ። አንድነት የሀገር ልዩ የክብር ጌጥ ነው።እንደ አሜሪካና ሌሎች የሰለጠኑ ሀገሮች በፌዴራሊዝም መርህ በነጻነት ራሳቸዉን እያስተዳደሩ በአንድነት ይተዳደሩ ማለቴ ነዉ፡፡ የፌዴራሊዚም መርህ የሚጠሉ ኃይሎች የፊዩዳሊዝም መንፈስ ተሸክመዉ ለአሃዳዊ አገዛዝ የሚታገሉ ለብዝበዛ የተሰለፉ የጭቆና ዝናር የታጠቁ የአንድነት የሰላም የዕድገት የነጻትና የዕኩልነት ጠላቶች ናቸዉ፡፡ የፌዴራሊዚም አስተዳደር ፍትህ አስተዳደር የአንድነት መሠረት ነዉ፡፡

ከዉጭ ኃይሎች የአገዛዝ ነዳጅ የሚመላለት የኢትዮጵያ ገዥመደብ በትጥቅ ትግል ወቅት ድምጹን ከፍ አድርጎ ስለ አማራ ቅኝገዥነት ያስተጋባ ነበር፡፡በ1991 ሥልጣን ከያዛ በኋላ ድምጹ ተዘጋ፡፡በዉሸት ፌዴራሊም ያልነቁ ሕዝቦችን እያታለለ በዴዲዎቹ እየተጠቀመ ከአማራ የጭቆና አገዛዝ እጥፍ ድርብ የሆነ ሕይዎት ቀርጥፎ የሚበላ የቅኝ አገዛዝ ቀምበር በቅኝ ተገዥዎች ላይ ጭኖ በዓለም ላይ የሌለ የግፍ ስቃይ በማድረሰ ላይ ይገኛል።በአማራና በወያኔ አገዛዝ መካከል ያው ልዩነት አማራ አሃዳዊ ቆራጭ ፈላጭ ሲሆን የወያኔ ፌዴሬሊዝም የውሸት ካባ የለበሰ አሃዳዊ ቆራጭ ፈላጭ ፌዴራሊም ነው። ሁለቱም በዝባዦች ጨቋኞች ገዳዮች ናቸው። ጭቁን ሕዝቦች የቅኝአገዛዝ ቀምበር ታሸክመዉ የሚሰቃዩ መሆኑን ተገንዝቦ ለህሊናዉ ተገዝቶ ለነጻነታቸዉ የሚታገሉ ሕዝቦችን ማሰሩን ማሰቃየቱን መግደሉን ማቆም ይኖርበታል፡፡ወያኔ ማወቅ ያለበት የነጻነት ትግልን ለጊዜዉ በጠመንጃ አፈሙዝ መገደብና ማብረድ ይቻላል፡፡ነገር ግን የነጻነት መንፈስ መግደል እንደማይችል ማወቅ አለበት፡፡ በጠምንጃ አፈሙዝ አፍኖ በእሳተ ገሞራ ላይ የተቀመጠ መሆኑን መርሳት የለበትም፡፡ ምክንያቱም ረመጥ በአመድ ቢዳፈን ሲገለጥ ረመጥ ይሆናል፡፡የነጻነት ትግል ረመጥ የሚያጠፋዉ በጠመንጃ ሳይሆን በነጻነት ብቻ ነዉ፡፡ሕዝቦች ሰብዓዊ ክብራቸዉ ተጠብቆ የሀገር ባለቤትነት መብታቸዉ ተከብሮ በነጻነትና በእኩልነት ቢኖሩ ለአመጽ የሚነሱበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ የአመጽ ፈጣሪ የግፍ በደልና ደም የሚያቃጥል ጭቆና ነዉ፡፡የኦሮሞ ሕዝብ አብዮት መነሻዉ ለ146 ዓመታት ደም አጥንትና ሕይዎት የሚያቃጥል ጭቆና ዉጤት፡፡አንድነት ጠልቶ ለመገንጠል ፈልጎ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ መረዳት አለበት፡፡ ተፈቃቅሮ ተከባብሮ ተስማምቶ በንድነት በነጻነት አብሮ መኖር አስፈላጊ ነዉ። አንድነት የሀገር ልዩ የክብር ጌጥ ነው።

በኦሮሞ ላይ የደረሰዉ የቅኝአገዛዝ በደል፡፡

ምንሊክ በእንግሊዚ በፈርሣይ በጀርመን በኢጣሊያን በሰዊዚና በሩሲያ ተደግፎ በአፍሪካ ምድር ገብቶ የማያዉቅ ዘመናዊ ጦር መሣሪያ ታጥቆ ለ7 ዓመታት ተደራጅቶ በእጃቸዉ ጦር ጎራዴ በስተቀር የረባ ጠመንጃ የሌላቸዉ ኦሮሞና ደቡብ ሕዝቦችን በመዉረር ቅኝተገዥ አደረጋቸዉ፡፡ከላይ እንደተገለጸዉ በዉጭ ኃይሎች የተደገፈበት ምክንያት ፓጋንና እስላም የሚባሉ ሕዝቦችን ሃይማኖት ለዉጦ የአፍሪካ ቀንድን የክርስቲያን ቀጠና ለማድረግ እንደ ነበር ሁኔታዎች ይመሰክራሉ፡፡የዉጭ ኃይሎች ገዥ መደቦቹን እስከ ዛሬ ድረስ እየመከሩ በፖለቲካ በሎጂሲቲክ በጦር መሣሪያ እያስታጠቁ የሚደገፉት የክርስቲያን ሀገር በእስላሞች እንዳይዋጥ ብለዉ ነዉ፡፡ ከሁሉም ሕዝብ በኦሮሞ ላይ ብዝበዛ ዘረፋ እስራት ግድያ ጭፍጨፋ መዓት እየወረደበት የሚኖረዉ ምስጥሩ የእስልምና ሃይማኖት ነዉ፡፡ በአጼ ዮሐንስ ቴዴሮስ የተጀመረዉ የሃይማኖት ጦርነት እስከ ዛሬ ድረስ ሥሙንና ዘዴዉን እየቀያየረ ኦሮሞን እየበላ ይኖራል፡፡

በ1868 ምንሊክ ከሰሜን ሸዋ ከአንኮበር ከተማ ተነስቶ በአራት አቅጣጫ በኦሮሞ ላይ ወረራ በአካሄደበት ወቅት እንደ ዛሬዉ የወያኔ አገዛዝ ግድያ ጭፍጨፋ የዘር ፍጅት ብዝበዛና ዘረፋ ይፋፋም ነበር፡፡ ወታደሮቹ ደመወዝ እንዲከፈላቸዉ ለምንሊ ጥያቄ ሲያቀርቡ ከድል በኋላ “ጋላን ትበላለችሁ” አርፋችሁ ተቀመጡ አላቸዉ፡፡ጋላን ገድለህ ሀገሩን ቀምተህ፤ንብረቱን ዘርፈህ፤ሃብቱን በዝብዘህ ብለዉ ተብሎ ስለተነገረዉ የተራቡ ወታደሮች በእያንዳንዱ ኦሮሞ ቤት ገብተዉ ከጓዳ ዱቄት ገልብጠዉ ወሰዱ፡፡የሴቶች መቀነትና የወንዶችን ኪስ በርብረዉ ገንዘብና ወርቅ ዘረፉ፡፡ሰንጋ ሙክት መሲና እየቀሙ አርደዉ መብለቱን ቀጠሉ፡፡የኦሮሞ ወንዶቹን በባርነት አሰልፈዉ እንጨት እንዲፈልጡ ቤት እንዲሰሩ፤አጥር እንዲገነቡ ልብስ እንዲያጥቡ እንደ ሴት እህል እየፈጩ ዱቄት እንዲያቀርቡ አደረጉ፡፡የኦሮሞ ሴቶች ወተት አልባዉ ቅቤ ንጠዉ እንዲያቀርቡ፤እህል ፈጭተዉ እንጄራ እየጋገሩ፤ወጥ እየሰሩ፤ልብስ እያጠቡ በባርነት እንዲያገለግሏቸዉ አደረጉ፡፡በዱላ እየደበደቡ በአለንጋና በጅራፍ እየገረፉ ተጫወቱባቸዉ፡፡እንስራ ተሸክመዉ ዉኃ ለመቅዳት በሚሄዱ የኦሮሞ ሴቶች ላይ የጥይት ኢላማ እየተማሩ ይገድሏቸዉ ነበር፡፡የአዉሮፓ ቅኝገዥዎች በአፍሪካ ላይ ያልፈጸሙትን ግፍ፤የምንሊክ ወራሪ ገበሬዎች ዘግናኝ ግፍ ፈጸሙ፡፡

በ1883 ምንሊክ ሸዋን ከየዘ በኋላ ማዕከሉ አድርጎ በአርሲ ላይ የዘር ፍጅት ፈጸም፡፡የወንዶች ግራ እጅና የሴቶች ግራ ጡት እየቆረጠ መቀጣጫ አደረጋቸዉ፡፡በሐረርጌ ጨለንቆ ላይ በመትረየስና በቦምብ ሕዝቡን ጨፍጭፎ በአሸነፈ ማግስት ወታደሮቹ ከኦሮሞ ሃብታሞች ቤት ገብተዉ 700,000 ማሪታሬዛ ዘርፈዉ ወሰዱ፡፡ ግዙፍ ገንዘብ ዓይተዉ ስለማያዉቁ ቆጥረዉ መከፋፋል አቃታቸዉ፡፡ እንደዚህ ሲቸገሩ 10 ማሪታሬዛ እየቆጠሩ 1 ጠጠር፤20 እየቆጠሩ 2 ጠጠር፤30 እየቆጠሩ 3 ጠጠር….100 እየቆጠሩ 10 ጠጠር እያስቀመጡ መከፋፈል ሲያቅታቸዉ እንደገና ለሳምንት ያህል ቆጥረዉ መከፋፈል ሲያቅታቸዉ ምርኮኛ ኦሮሞዎችን ጠርተዉ አስቆጥረዉ እንደተከፋፈሉ ታሪካቸዉ ይናገራል፡፡እንደዚህ ያሉ ገንዘብ ቆጥረዉ መከፋፈል የማይችሉ ኋላቀር ጨካኞች ናቸዉ የዘር ፍጅት የፈጸሙት፡፡ኦሮሞን ከአሸነፉ በኋላ ሀገሩን ቅርጫ ተከፋፍለዉ ሕዝቡን በቅኝአገዛዝ ቀምበር አስረዉ ገባር ጭሰኛ አሽከር ገረድ አድርገዉ እስከ የካቲት 66 አብዮት ድረስ አጥንቱን ግጠዉ ደሙን እየመጠጡ ይኖሩ ነበር፡፡አብዮቱ የነፍጠኞች ሕይዎት እጅና እግር እየቆራረጠ መሠረታቸዉን ነቅሎ አጠፋ፡፡

የቅኝአገዛዝ መስራችና የጭቆና መሪ የነበረዉ ምንሊክ ነሐሴ 17, 1844 በሰሜን ሸዋ አንጎሎላ በሚባል ቦታ ተወለደ፡፡ህዳር 3,1989 ንጉሠ ነገሥት ተብሎ ዘዉድ ጫነ፡፡ ከመጋቢት 10, 1889 ጀምሮ እስከ ታህሣሥ ወር 1913 እለተ ሞቱ ድረስ ኢትዮጲያን ሲገዛ ኖረ፡፡ኢትዮጲያ ለዓለም በአዋጅ ያሳወቀዉ ጥቅምት 25 ቀን 1907 ነበር፡፡በደምግፊት ጭንቅላቱ ተመቶ ሰዉነቱ ሽባ ሆኖ ለብዙ ዓመታት የአልጋ ቁረኛ ሆኖ ሲሰቃይ ከቆየ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተሰናበተ፡፡በሞት ሃፋፍ ላይ እያለ ሴት ልጁ የወለደችዉ ኢያሱ ሚካኤል ሥልጣኑን እዲወርስ በንዛዜ አሳወቀ፡፡ኢያሱ ሥልጣን ይዞ ሀገር በማስተዳደር ላይ እያለ የአማራ እሌቶች እስላም የክርስቲን ሀገር ማስተዳደር የለበትም ብለዉ አደሙበት፡፡በወቅቱ የኢትዮጲያ ሞግዚት ለነበረችዉ ፈረንሣይ ደብዳቤ ጽፈዉ ከስልጣን እንዲወገድ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ፈረንሣይ ተባብራ ኢያሱን እንዲወገድ ከአደረገች በኋላ ተፈሪ መኮንን አልጋ ወራሽ ሆኖ ተሾመ፡፡ኢያሱ ኦሮሞ በመሆኑ ሳይሆን በእስልምና ምክንያት ነበር ከሥልጣን ተባሮ ከታሰረ በኋዋላ በአስር ቤት እያለ የተገደለዉ፡፡

የሃይማኖት ጦርነት ታሪክ

የሃይማኖት ችግር ከጥንት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ መሆኑን ታሪኩን ያልተረዱና ምስጥሩን የማያዉቁ ሰዎች ኢትዮጵያ የሃይማኖት ችግር የለባትም እያሉ ይናጋረሉ፡፡ምንሊክ የክርስቲያን ደሴት ኢትጵያ እንዲጠብቅ አርዱኝ እያለ ለአዉሮፓዊያን መፈክር ያሰማ የነበረዉ በዙሪያዉ የከበበዉን የእስልምና ባሀር ስለሚያዉቅ ነዉ፡፡ገዥዎቹ ሃይማኖታቸዉ ክርስቲያን በመሆኑ ምክንያት ከዉጭ ኃይሎች የማያቋርጥ የሎጂስትክ የትጥቅና የሞራል ድጋፍ እያገኙ ጡንቻ አፈርጥመዉ ከዉጭ ምንም ደጋፊ የሌላቸዉ ሕዝቦችን እየጨፈጨፉ የሚገዙት ምስጥሩ ሃይማኖት ነዉ፡፡፡ከዉጭ ኃይሎች ድጋፊና ጠመንጃ ባይኖራቸዉ ጭቁኖችን ለአንድ ቀን በጉልበት መግዛት አይችሉም፡፡አበሲኒያዊያን በዉጭ መንግሥታት ተጠግተዉ መኖር የጀመሩት ከኢዛና ዘመን ጀምሮ ነዉ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ከጥገኝነት ተላቀዉ ራሰቸዉን ችለዉ የኖሩበት ዘመን የለም ፡፡

በ16ኛ ክፍለ ዘመን ፖርቱጋል የክርስቲያን ሀገር ከእስላሞች ወረራ እጠብቃለሁ ብላ ከአበሲኒያ ጎን ተሰልፋ ኦሮሞን ወግታ የአበሰኒያ የበላይነት ከአረጋገጠችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በዉጭ ኃይሎች ተደግፈዉ ይኖራሉ፡፡ለ500 ዓመታት ያህል በኦሮሞና በአበሰኒያ መካከል ሲካሄድ የኖረዉ የዘመናት ጦርነት ምንጩ ሃይማኖት ነበር፡፡ አጼ ዮሐንስ4ኛ አጼ ቴዎድሮስ በአንግሊዝ እየተደገፉ በዋሎ ሙስሊሞች ላይ የዘር ፍጅት የፈጸሙት በሃይማኖት ምክንያት ነዉ፡፡በአፈለዉ ጊዜ እንደገለጸኩት ቴዎድሮስ የዋሎ ሙስሊሞችን አፍንጫ ከንፈር ምለስ አንገት እግርና እጅ እየቆረጠ እጃቸዉን በአንገታቸዉ ላይ አንጠልጥሎ “ሄዱ ለመሐመዶቻቸሁ አሳዩ” ብሎ ላካቸዉ፡፡ሌሎች 43 ሰዎችን ቆራርጦ ፈጃቸዉ 21 ተዋቂ ሰዎችን ከነሕይዎታቸዉ ገደል ዉስጥ ጥሎ ገደላቸዉ፡፡ ሕዝቡን በበረት ዉስጥ አስሮ በበዝናብ ቀን በጻሃይ ሌሊት በብርድ ተሰቃይተዉ እንዲያልቁ አደረገ፡፡የብርቱካን አትክልቶቻቸዉን ጨፍጭፎ በሰብሎቻቸዉ ላይ እሳት ለኮሶ አወደመ፡፡ከብቶቻቸዉን አርዶ ስጋ እንደ ተራራ ክምሮ ያራዊትና የአሞራ ቀለብ አደረገ፡፡ የዚህ ሁሉ መዓት ሰበቡ ያልታወጀዉ የክሩሴድ ጦርነት ነበር፡፡

አጼ ዮሓንስ (ካሣ ምርጫ)የዋሎ ሙስሊሞችን አንድ ላይ ሰብስቦ ሁለት ቦታ ከፍሎ ቄሶችን ጠርቶ ጠበል ረጭተዉበት በስተምስራቅ ያሉትን ወልደ ማሪያም፤በስተ ምዕራብ ያሉትን ወልደ ሚካኤል ብለዉ ክርስትና እንዲቀበሉ አደረጉ፡፡ ክርስትና ከተቀበሉ በኋላ ተደብቀዉ ሲሰግዱ የተገኙት ሙስሊሞች ተይዘዉ ሲጠየቁ “ዎላሂ ክርስቲያን ነን” አሉ ተብሎ እስከ ዛሬ ድረስ ይነገራል፡፡“ክርሰቲያን ሆኖ ዎላሂ የሚል የለም” ተብለዉ ቅጣት ተፈጸመባቸዉ፡፡ከፍጅት የተረፉ ክርስትና አንቀበልም ያሉ ወደ ሱዳን ሸሽተዉ አመለጡ፡፡ዘለዓለም መዓት እየወረደበት የሚኖር ከሃይማኖት ባርነት ነጻ ወጥቶ መከፋፈሉን አቁሞ አንድነቱን ጠብቆ መታገል አለበት፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ትግል ደጋፊ አጥቶ አቅመ ደካማ ሆኖ የሚኖርበት ምክንያት ሃይማኖት መሆኑን የሚከተከለዉን መረጃ ያረጋግጣል፡፡

“The majority Oromo are Sunni Muslims, some of them Christian and the rest are adherent to the tradition to Cushitic religion. The Oromo Liberation Front and United Oromo Liberation Front have declared an armed struggle seeking their independence imposition of Islamic law in Ethiopia that one of the first Christian land in the Africa.” Source, Encyclopedia of African American experience, page 996-7

በአማሪኛ ሲተረጎም አብዛኞቹ ኦሮሞዎች ሱኒ ሙስልሞች ናቸዉ፡፡ጥቂቶቹ ክርስቲያን ናቸዉ፡፡የቀሩት የጥንቱ የኩሽ ባህል ሃማኖት ተከታይ ናቸዉ፡፡የኦሮሞ ነጻነት ግምባርና የኦሮሞ አንድነት ነጻነት ግምባር፤ከአፍሪካ የመጀመሪያ ክርስቲያን በሆነች እትዮጵያ ላይ የእስላም ህግ ለመጫን የትጥቅ ትግል አወጁ”“ ይላል፡፡ይህ የወያኔ መልእክት ሳይሆን አይቀርም፡፡ኦነግ ሔራዊ ነጻ አዉጭ ግምበር ነዉ እንጂ ለሸርኣ ህግ የሚታገል ድርጅት አይደለም፡፡የኦሮሞ ነጸነት ትግል ተዳክሞ የቅኝ አገዛዝ ቀምበር መስበር ያቃተዉ በዚህ ምክንያት ነዉ፡፡እጅግ በጣም አድርጎ የሚያሳዝነዉ የገዥ መደቦቹ የዘመናት የግፍ ጭቆና ብቻ አይደለም፡፡ከትዉልድ ትዉልድ በሃይማኖት ምክንያት መዓት እየወረደበት እንደ እባብ አናቱ እየተቀጠቀጠ በቁመናዉ እየተቃጠለ እየወደመ የሚኖር ሕዝብ በሃይማኖት ልቡ ተራርቆ መግባበት አቅቶት ተከፋፍሎ አንድነቱን እየበላ መኖሩ ነዉ፡፡ታሪክ ያስተምራል ዘመን ይመክራል ጊዜ ይለዉጣል፡፡ኦሮሞ ምክር ተቀብሎ አአምሮዉን ለዉጦ ከሃይማኖት አስር ቤት ነጻ ወጥቶ አንድነቱን ጠብቆ መኖር አለበት፡፡ከደረሰበት የዘመናት ዉድቀት ተምሮ ሃይማኖት በኪሱ አንድነት በደምና በሕይዎቱ ጠብቆ ለትዉልድ ማስተላለፍ አለበት፡፡ በሃይማኖት ምክንያት የቅኝ አገዛዝ ባርነት ስር ወድቆ ሀገሩ ተይዞ ከትውልድ ትውልድ መዓት እየወረደበት የዘር ፍጅት እየተፈመበት እየተበዘበዘ እየተዘረፈ በድሀነት እየማቀቃ የሚኖር ሕዝብ በሃይማኖት ምክንያት ተቃቅሮ መተማመን አቅቶት ተከፈፍሎ ያለአንድነት መኖሩን ማቆም አለበት። በጭራሽ መከፋፈል የለበትም ያለአንድነት ራቁቱን ማደር የለበትም፡፡

ማጠቃላያ፡- መጽሐፍ ቅዱስ ቁርአን ጫትና የወያኔ ስንክሳር ብቻ የሚያነቡ ሰዎች የኦሮሞ የታሪክ ጭማቂ እየጠጡ መጽሐፍ እንድያነቡ ቤተክርስቲያንና መስኪድ ገብታችሁ ምከሩአቸው አሳውቋቸው ቀስቅሷቸው። ታሪኩን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሕዝብ ሞራሉ ይገነባል ማንነቱን ያውቃል አንድነት አጥብቆ ለማንም የማይበገር ኃያል ይሆናል። ታሪኩን ማንነቱን አንድነቱን የማያውቅ እንደ እንስሳ ደካማ ልፍስፍስ ሆኖ እየተረገጠ ሀ ይኖራል። ስለዚህ ኦሮሞዎች መጽሐፍ የማንበብ ባህል ማዳበር አለባቸው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ታሪክ እንዲያነብ አስተላልፉ፡፡ ኦሮሞዎች እንደ ብሔርተኛ ካድሬ ለሕዝብ አስተምሩ፡፡የአፍሪካ የቅኝአገዛዝ ካርታ ሳይሰራ በ1646 ዓመተ ምህረት ሀገሩ ካርታ ያለዉ መሆኑን አሳዉቁ፡፡ ደበተራዎች ደናቁርት ፕሬፌሰሮች እንደሚያናፍሱት ኦሮሞ በጦርነት ተስፋፍቶ ሰፊ ሀገር የያዘ ሕዝብ አይደለም፡፡ከታች ብዙ ዓለም አቀፍ ካርታዎች እንደሚያረጋግጡት ከ8000 BC ኩሽ እየተባለ ሲጠራ የኖረዉ ኦሮሞ በ1600 AD ጋላ ተብሎ መጠራት ጀመረ፡፡ከሰሜን እትዮጵያ ተነስቶ ወደ ደቡብ በመስፋፋት መላዉን ኢትጵያ ይዞ ሱማሌን አጠቃሎ ይኖር እንደ ነበር ታሪክ ይመሰክራል ካርታዎቹ ያረጋግጣሉ፡፡ኦሮሞ ሌላ ሕዝብ ባልነበረበት የጨለማ ዘመን ደኖችን እየመነጠረ እስከ ሱማሌ ድረስ ተስፋፍቶ ኖረ እንጂ በጦርነት አልተስፋፋም። በጦር የተዋጋቸው የዱር አራዊቶችን ብቻ ነበር።ሱማሌ ከሲማሌ የመጣ የኦሮሞ ባላባት ሥም ነው። በ 16ኛ ክፍለ ዘመን 5 ጎሳዎች ተሰባስው ሱማሌ የሚባል ሀገር መሠረቱ።ኦሮሞ የሱማሌ ሕዝብ ማህጸን ሀገሩን የቆረቆረ መሆኑን ታሪክ ይናገራል። ዛሬ የኦሮሞ አንድነት እየበጠበጡ የሚንጡ እንደሱማሌ ጎጠኞች ሕዝብ የሚያውኩ ግለሰቦች የሱማሌ በህል የወረሱ ሳይሆን አይቀርም።

መረጃ፡- ከካርታ 1) ጀምሮ ካርታ 2) ካርታ 3) ካርታ 4) ካርታ 5) ካርታ 6) ተመልከቱ፡፡ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥም ኩሸይት ነበር፡፡፡ኢትዮጵያ ማለት ኦሮሞ ማለት ነዉ፡፡ ኦሮሞ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዘር ማህጸን ነዉ፡፡ከኦሮሞ ያልተፈጠረ አንድም ሕዝብ የለም፡፡ ሴሜቲክ ናይሎቲክ ኦሞቲክ ኩሸቲክ የሚባሉ ነገዶች ከኦሮሞ የወጡ ናቸዉ፡፡ የአፍሪካ ¾ ሕዝብ ያቀፈዉ ባንቱ በ3000 BC ገደማ ከኑቢያ ግዛት ከኩሽ-ኦሮሞ የተገነጠለ መሆኑን 7 የUNESCO የጥናት ሰነድና የታሪክ መረጃዎች ያረጋግጠሉ፡፡ የባንቱ ታሪኩን ወደፊት ለሕዝብ አቀርባለሁ፡፡ኦሮሞ የሰዉ ዘር ግንድ የታሪክ መሠረት የአፍሪካ አባት መሆኑን ለዓለም ታሪኩን አስታወቁ፡፡

ሁል ጊዜ እራሴን እየጠየቁ የሚገርመኝ የኦሮሞ ዶክተሮች ፕሮፌሰሮችና ሌሎች ምሁራኖች ኩሽ የሚባል ኦሮሞ መሆኑን ፤ኦሮሞ የሰው ዘር ግንድ የአፍሪካ አባት መሆኑን ለምን አላወቁም ? ለብዙ ዘመናት ተቀብር የኖረው እንደ ኦሮሞ ሀገር ካርታ ፤ንግሥት ጉዲት ፣ንግሥት ማኪዳ፣ ዛጉዌ ፤ግዕዝ የአክሱም ሥልጣኔ ፤የፋሲል ግምብና የቅኝ አገዛዝ ታሪክ የመሳሰሉ ግዙፍ ታሪኮችን ከመቃብር አውጥተው ለሕዝብ ማሳወቅ ለምን አቃታቸው?
Bena Bulto