Fayyaan Mataa, Fayyaa Waa Maraa ti!

ኢሬቻን መረዳት

በአባ ሚራ

“የምስጋናና ትህትና ስነ ስርአት
የንጽህናና የብልጽግና ክብረ በዓል፤
የአብሮነት፣ አንድነትና የፍቅር ነጋሪት፤”

~~~

እሬቻ ማለት ምንም እንኳን ቀጥተኛ የአማርኛ ትርጉም ባይኖረውም ‘ምህለላ’ ምስጋና’ የሚለው የቃል ፊቺ ይገልጸዎል። በዋቄፈና ስርአትም ይህ ባህላዊ የምስጋና ቀን ከዘመን መለዎጫ ጋር የተቆራኘና ከወቅቶች ሽግግር እንደየ ኢሬቻ አይነት ይለያያል።
በመሆኑም እሬቻ የኦሮሞ ህዝብ የባህል፣ማንነትና፣ እምነት እሴቶች የያዘ ጥልቅ የአገርና የዓለም ትሩፋት ነዉ። ኢሬቻ በወቅትና በቦታዎች ስናየው በሁለት ይመደባል :-

#ኢሬቻ_መልካ /ኢሬቻ ብራ

የመርበብ ምስጋና በእውቅ ቦታዎች በውሃ ሙላቶች
ላይ የሚከናወን ሲሆን፣ በአዲስ አመት አልያም ከክረምት ወቅት ወደ በልግ ወቅት የሽግግር ወቅት በጠራና በተረጋጋ የምንጭ ውሃ ቦታዎች የሚፈፀም የምስጋና ስርአት ነው።
ይህም በአብዛኛው በወርሃ መስከረም ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ሳምንት ይፈጸማል። በስፋት በአውራ የምስጋና ቦታዎች ቢሾፍቱ ሃይቆች በአርሰዴ የሚፈፀመው ታላቁ ማሳያ ነው።

#ኢሬቸ_ቱሉ / ኢሬቻ አርፋሳ

ይህ የምስጋና ቦታ ከስሙ እንደምንረዳው የተራራ(ቱሉ) ላይ ምስጋና ነው። በወቅቱም በቦታም በተቃራኒው ጊዜና ቦታ ይደረጋል። ይህ ምስጋና ከበጋ ወደ ፀደይ መግቢያ የተራሮች ልምላሜና አሮንጒዴ መጀመሪ ወቅት ነው። ከአምቦ 60 ኪሎ ሜትር በጂባት የተራራ ሰንሰለቶች ላይ የሚፈፀመው አንዱና ታላቅ የምስጋና በአል ነው።
ዛሬ ላይ በቢሾፍቱ፣ የሆራ ሀርሰዲ እሬቻ መልካ በመላ ኦሮሞ የሚከበር፣ የኦሮሞ ብሄራዊ ክብረ በዓል ነዉ። ቢሄራዊ ክብረ ባአላት ሃይማኖታዊ አልያም ሀገራዊ በአላት ሊሆኑ ይችላሉ። መስቀል፤ ጥምቀት፤ፋሲካ፤ ኢድ አልፈጥር ፣ኢድ አላዳሃ…ከሃይማኖታዊ ባአልነት በጅጉ ባልተናነሰ የመላ ኢትዩጵያ የባህልና ስነ ህዝብ ባህሪያት ነጸብራቅ እሴቶቻችን ናቸው። በተመሳሳይ እንደ ቢሄርና ቢሄረሰቦች መገለጫ ኢሬቻ ፤ ጫምበላላ፤ አሸንድየ/አሸንዳ/ሶለንና የመሳሰሉ ሌሎች ቢሄራዊ በአላት የየክልሉ በአላት ከመሆነ የመላ አገሪቱ ቡሎም በአለም የቱሪስት መስህብነት የወል ማንነታችን መገለጫ ወደ መሆን ማበልጸጉና አገራዊ እውቅና ለመስጠት መትጋት ተገቢ ነው።

#እሬቻ የፖለቲካ ትሩፋት መገለጫ አይደለም።

ኢሬቻ በፖለቲካ እና በሃይማኖት አመለካከት እና እምነት የተወሰነ ባለቤት ያለው በዓል አይደለም። በክርስትያንና በሙስሊም እንዲሁም በኦሮሞ ዋቄፈታዎች የእኩልነት የአንድነት በአል ነው። ምናልባትም ሁሉም ሃይማኖቶች በተናጥል ከነበራቸው የምስጋና ጊዜና እለት በአንድነት የሚገናኙበት ባህላዊ የምስጋና ስርአት ኢሬቻ ብቻ ነው።
ከጥቂት ጊዜት ወዲህ የኦሮሞ የትግል ማቀንቀኛና የኢትዮጵያ መንግስታት ጥላቻና የትግል አማራጭ ወደ መሆን የመጣ ቢሆንም በየትኛውም አለም ህዝባዊ በአላት እንዲቀጭጩ አልያም ለፍረጃ መዳረግ አልያም ለፈጣሪ ቶኪቻ ዎቃ የሚደረግ ምስጋናን ወደ ሰልፍና ተቃውሞ መቀየር ተገቢ አይደለም። በተለይ በ2009 የተከሰተው የሞት እልቂት አደጋ ዘግናኝና እጅግ አጠልሺ ነበር፤ አለማቀፋዊ እውቅናም ሊቸረው የነበረውን ተነሳሽነት አጠልሽቶ አልፏል። በተቃራኒው የ2010 የተሳካ በራሱ በባለቤቱ ህዝብ ከሰላም እስከ ስነ ስርአት ክንዎኔ በተሳካ ተፈጽሟል።
በያዝነውም አመት የሚከበረው እሬቻ በሀዩ፣ በአባ ሙዳ፣ በአባ ቦኩ፣ በሃdha ሲቄ እና በፎሌዎች ሰላም ማስከበር ሰላምና ወግን በያዘ ምርቃት ይደምቃል፤

#በመንጻት ቀንም የአባቶች ምርቃት

ጥላቻ ፤ ቂምና በቀል በናንተ ዘንድ ቦታ አይኑረዉ፣
የወጣው በሰላም ይግባ የገባው በሰላም ይረፍ ሰላም ለናንተ ሁሉ፣ ለወገን ሁሉ ይሁን፣
ሰላም ለምድር ይሁን፣
ሰላም ለፍጥረት ሁሉ ይሁን፣
በዚህም በዋቃ ፊት በምስክርነት ቁሙ፤
በእሬቻ አባቶችና እናቶች፣ ቄሮ-ቀሬ ያለፈዉን ዘመን ከአዲሱ ዓመት ጋር እያገናኙ ዋቃን ያመሰግናሉ፣ ያቅዳሉ። የዘንድሮዉ እሬቻ፣ እሁድ፣ መስከረም 20፣ 2011 ዓ.ም ሲከበር፣ ምስጋናና እቅድ ይኖረዋል። ያድርሰን፣ እንገናኛለን፣ እንሰማለን!

#ሁላችንም ለምስጋና ተጠርተናል!
ፈጣሪ አገራችንን ሰላምና ፍቅር ያብዛላት!!