Fayyaan Mataa, Fayyaa Waa Maraa ti!

የሁለቱ ወንድማማቾች ወግ

በደራራ ዳዲ

“ሁለቱ ወንድማማቾች” በመባል በኢትዮጵያ ታርክ ዉስጥ የምጠቀሱት መንግስቱ ና ገርማሜ ንዋይ ናቸዉ። እኔ ግን ያማነሰዉ እንሱን አይደላም። ቦጅ፤ ወሌጋ የተወለዱና ያደጉ ቦሃላም ታላቅዬዉ በሀይማኖት ዘርፍ ታናሽዬዉ ደግሞ በፖለትካ ዘርፍ አሻራቸዉን በኢትዮጵያና በተለይም በኦሮሞና ኦሮምያ ላይ ላኖሩት ጉድና ቱምሳና ባሮ ቱምሳ ነዉ። የነዝህን ወንድማሞች ታርክ ለማስታወስ ካልሆነ በቀር እንድሁ በ አጭሩ ተጽፎ የምያልቅ ታርክ አይደላም ያላቸዉ።

ጉድና ቱምሳና ባሮ ቱምሳታድያ በፌስቡክ ዘመንም እናስታዉሳቸዉ ዘንድ ዊክፐድያ ላይ ስለነሱ ፈለግኩኝ ቄስ ጉድና ታላቅ ወንድም ናቸዉ። ባሮን በሀላፍነት ያሳደገዉ እሱ ነዉ። ቄስ ጉድና በCivil right movement ግዜ አመርካን ሀገር መጥቶ ተምሯል። አፍርካ ሀገር ዉስጥ በመዘዋወር ሀይማኖታዊ ትምህርትን ተከታትሏል እንድሁም አስተምሯል። በCivil right movement ግዜ የዜር አድሎ በ አመርካ ብቻ ሳይሆን በኢትዮፕያም መኖሩን ሳይገነዜብ አልቀረም።

ከደርግ ጋር ፍቅር የላቸዉም። ይህም የሆነዉ ቄስ ጉድና እንዴ ለሎቹ ቄሶች አጎንባሽ አልነበሩም። ለጭቁን ህዝብ የቆሞ ነበሩ። የታንዛንያዉ መሪ ጁልዬስ ነረሬ “ይህ ሀገር ላንቴ አይሆንም፤ ከዝህ ዉጣና ና በሀገሬ በነጻነት ኑር” ብሎት ነበር። ቄስ ጉድና ግን “ሀገረን፤ ህዝቤን ጥዬ የትም አልሄድም የመጣዉን እዝሁ እቀበላለሁ” በማለት ግብዣዉን አልተቀበሉም። 1979 አ.ም ደርግ ወስዷቸዉ ደብዛቸዉን አጠፋቸዉ። ደርግ እስክያጠፋቸዉ ድረስ የመካነ፡ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ፕረዝዳንት በመሆን ያገለግሉ ነበር።
ታናሽ ወንድሙ ባሮ ቱምሳ ደግሞ የታወቁ ፖለትከኛ ናቸዉ። በህግ ና በፋርማስ ድግር አላቸዉ። በነግራችን ላይ Science and Art አንድ ላይ የምገርም ትምህርት ነዉ።

የኢትዮጵያ ጭቁኖች አብዮታዊ ፓርቲ የምባለዉን በምፍጠር እኔ ምኤሶን፤ ኢሀፓና ለሎች ድርጅቶች ስጨፈለቁ የሱን ፓርቲ ግን በተወስኔ ደረጃም ብሆን ከመመታት አድኗል። ዛሬ ከፌስቡክ ላይ የምጨፍሩት እንደነ አሰፋ ጫቦንም አሳምኖ የፓርትዉ አባል አድርጓል።
ካሳ ታደሴ የጀነራል ታደሴ ብሩ ልጅ (ነብሱን ይማርና) ከአስር አመት በፍት እንድህ ብሎኝ ነበር። “ባሮን ከልጅኔት ጀምሮ አቀዋለሁ። አባቴም በጣም ይወደዉ ነበር። ኦሮሞን መምራት የምችል ሰዉ ነዉ ይለዉ ነበር” አለኝ።

ባሮ ኢጭአፓ ብቻ አይደላም የመሰረተዉ። ከኦነግ ምስረታም የአንበሳዉን ድርሻ ይይዛል። ከአሰፋ ጫቦ በስተቀር ሁሉም የኢጭአፓ አባላት የኦነግ አባል ነበሩ። የደርግ ሁነታ አላስቀምጥ ስላቸዉ ወዴ ጫካ ትግል ገቡ። የ አጋጣም ነገር ሆኖ በገዛ ጓደኛቸዉ በድንጌት ተሰዉ።
ስለ ባሮ ለማወቅ የመንግስቱ ሀይለማረም፤ የፍቅረስላሴ ወግደረስ ና የብዙዎቹን የደርግ መጽሀፍቶችን ብታገላብጡ በሰፍዉ ታገኙታላችሁ።

ፍቅሬ ስላሴ ወግደረስ በ ገጽ 357 ላይ ስለ ባሮ እንድህ ብሏል። “ባሮ ቱምሳ የመደብ ሳይሆን የብሄር ጭቆና ነዉ ያለዉ ብሎ ያምናል። ሰላማዊ ትግል እንደ አጋጣም በመጠቀም ሁሉም ክፍለሀገር ዉስጥ ካድሬዎችን ለኦነግነት መልምሏል። በተለይ በ አርሲ ና በባሌ ሰፍ ካድሬዎችን በመመድብ ያለዉን መስርያበት ተቆጣጥረዋል። በኢጭአፓ ዉስጥ ያሉትን ብቻ ሳይሆን በምኤሶን ዉጥ ያሉትንም ለብሄር እንቅስቃሴ መልምሏቸዋል። በድርጅት ና በሀሳብ ብቻ ሳይሆን በግል ደረጃ ባሮ ቱምሳ ና ሀይሌ ፍዳ በጣም ወዳጅ ናቸዉ”። በማለት የባሮን ታርክ ይዘረዝራል።
ሁለቱ ወንድማሞችን ጌታ በገነት ያኑራቸዉ።