Fayyaan Mataa, Fayyaa Waa Maraa ti!

#የአማርኛ_የበላይነት – #ያጋጣሚ” ብሎ ነገር!

By Tabsaayee Dheeressaa

ብዙዎቻችን እንዳየነው በአንድ #የዋልታ “መረጃ-ቲዩብ” ፕሮግራም (ቃለ-ምልልስ) ላይ አስተናጋጁ እንግዳውን (ፕ/ር እዝቄል ገቢሳን) “ለምሳሌ አማርኛ #ያጋጣሚ_ጉዳይ_እንጂ ሆን ተብሎ ገዢው መደብ ያንተ ቓንቓ ብሎ የደፈጠጠበት ሁኔታ አለ ወይ?” ብሎ ይጠይቃል
ፕ/ር እዝቄል በሌሎች ጉዳዮች ላይ በአጥጋቢ ሁኔታ መልስ ሰጥቶት እዚህች (ቓንቕ) ላይ ግን የተዘናጋ ይመስለኛል። “አጋጣሚ ይሁን በሂደት ግን ሆኖአል” የሚል ነበር የፕ/ር እዝቄል መልስ።

ሃቁ ግን ይሄ አይደለም። በተለይም (የአንድ ህዝብ የማንነቱ መሠረት የሆነው) የቓንቓ ጉዳይ በፍፁም #የአጋጣሚ_ጉዳይ አልነበረም። ዝርዝሮች ውስጥ መግባት ረዥም ጊዜ ሊወስድ ይችላል። በአጭሩ ግን:-

1. ምኒልክ “ከቤተክርስቲያን ቓንቓ በስተቀር ሌላ ቓንቓ መናገር #ወንጀል ነው” ብሎ አወጀ። ይህ አዋጅ ከምንም በላይ፣ ከዬትኛውም አካባቢ ይበልጥ #የወሎን_ኦሮሞ ክፉኛ ጎድቶአል። የዚህን አካባቢ ኦሮሞ ከማንነቱ ከኻያ ከገደብ ባለፈ መልኩ አመንምኖታል። አንድ ምሳሌ ብቻ ልማት – #ተስፋው_መሃመድ ይባላል። ዛሬም በህይወት አለ ብዬ እገምታለሁ። እኔና ተስፋው በደርግ ዘመን ማብቂያ አካባቢ በዩኒቬርሲቲ አንድ ባች፣ አንድ ዲፓርትሜንት፣ አንድ ዶርሚታሪ ነበርን። ለኔ ይህ ጊዜና ቦታ (ዩኒቬርሲቲ) ስለብሄራዊ ማንነቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓይኔ የተከፈተበት ነበር – ከምንም በላይ #ሽንት_ቤቶች ውስጥ ስለኔና ስለህዝቤ ከተፃፉት ስድቦች በመነሳት በዚህ ደረጃ #ወሎም_ኦሮሞ መሆኑን ተረድቻለሁ። አብሮ ከመቆዬት የተነሳ አንድ ቀን ተስፋውን “እስት የትውልድ ሃረግህን ቁጠርልኝ” አልኩት። በአባቱ ጀመረና “መሃመድ – ዓሊ – ገለታ – ገደባስ” ሲል “በቃኝ” አልኩትና፣ “እስቲ በናትህ በኩል ደግሞ ጥራልኝ” ብዬ ጠየኩት። ብዙም ሳንለፋ የናቱ ወገን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ኦሮሞ ሆኖ ቁጭ አለ። የናቱ ስም “ምናምን/እገሊት ዋቀዮ” ነውን
#ተስፋው_መሃመድ ግን እስከዚያች ሰዓት ድረስ #ኦሮሞ መሆኑን አያውቅም ነበር። በዚህ ሁኔታ ማንነታቸው የጠፋ የኦሮሞ ልጆችን እስቲ እንገምት።

2. ስለ ሌላው አላውቅም – በኦሮሚያ አካባቢዎች ግን (እስከድርግ ስርዓት መምጫ ድረስ) በት/ቤቶች ጊቢ ውስጥ ኦሮምኛን ማውራቱ ይቅርና በስህተት አንዲት የኦሮምኛ ቃል መጠቀምም #ክልክል ነበር፣ የተከለከከ ነበር። ይህም መንግሥታዊ #ፖሊሲ ነበር። ለዚህ ደግሞ አሻራውን የተሸከሙ አንዲት ህያው ምስክር (ዛሬም በህይወት) አሉ። ት/ቤት ጊቢ ውስጥ እያሉ (ያኔ የሴት ኮረዳ፣ የዛሬዋ አዛውንት) በድንገት አንድ ወይም ሁለት የኦሮምኛ ቃል ከኣፋቸው ይወጣል። ይህ ነገር ለት/ቤቱ ሃላፊ ሪፖርት ይደረጋል። ሃላፊው አርጩሜ ወስዶ ኮረዳዋን በእጅዋ መዳፍ ውስጥ ሲገርፍ አርጩሜው የኮረዳዋን መዳፍ ቆርጦ ገባ። ኮረዳዋ (የዛሬዋ ባልቴት) ዛሬም ጠባሳውን በእጅዋ መዳፍ ውስጥ ተሸክማለች።

3. “ገመድ-ኣፍ ጋላ” የሚሉትን የማንቓሸሻ ስድብ፣ typical/ትክክለኛ የቅኝ ገዢዎች የስነልቦና ጦርነት ጥይት ለመሸሽ ሲሉ በተለይም ለጊዜያዊ ጉዳዮች (ለምሳሌ ለንግድ) ወደመሃል አገር ሲመጡ ራሳቸውን ለጊዜው (temporarily) #ድዳ የሚያደርጉ ኦሮሞዎች ነበሩ። ለዚህም በህይወት ያሉ (ቢያንስ አንድ) ህያው ምስክር አለኝ። ሃሩን እድርስ ሙሳ ይባላሉ። በአሁኑ ወቅት ስቶክሆልም፣ ስዊድን ይኖራሉ።

ለነገሩማ ድንቁርናቸው ገደብ አጥቶ እንጂ የሰው ልጅ ሆኖ ተወልዶ “#ገመድ_እፍ” የሚባል ነገር የለም። አንድ ሰው ከኣፍ መፍቻ ቓንቓው (ከnative/mother tongue) ውጪ በሁለተኛና ሦስተኛ ቓንቓነት የሚማራቸውን ሌሎች ቓንቓዎች አወላግዶ መናገር ሳይንስ ነው፣ ሳይንሳዊ ነው፣ ስነልሳናዊ/linguistics ነው፣ እንጂ የግለሰብ ወይም የማህበረሰቡ ተፈጥሮኣዊ እንከን/ጉድለት አይደለም። ምክንያቱም (ባጭሩ) የግለሰብ የኣፍ መፍቻ ቓንቓው ስነ-ልሳናዊ ባህሪያት/linguistic features በዚያ በሁለተኛው፣ በሦስተኛው ቓንቓ ላይ ይንፀባረቃሉ፣ ተፅእኖ ያደርጋሉ። ይሄው ነው።

በነገራችን ላይ Obbo Haruun በዚሁ እና በሌሎችም የዘር መድሎዎች ሆድ ብሶአቸው በመጨረሻ ሁሉን ነገር ጥለው ጫካ ገቡ፣ ኦነግን ተቀላቀሉ። እዚያም (በመጨረሻ ኢህአዴግ/ኦፒዲኦ እጅ ወድቀው ለ12 ዓመታት እስከታሰሩ ድረስ) በበረሃ ከተራ ወታደርነት እስከ ወታደራዊ-ካድሬነት በመሳተፍ በህዝባቸው የነፃነት ትግል ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።
FB ላይ በመሆኑ እንጂ ሌሎች በርካታ ታሪካዊ መረጃዎችንም መጨመር ይቻላል። ነገሩ ባጭሩ ይህን ይመስል ነበር፣ እንጂ #ያጋጣሚ አልነበረም።